Thursday, May 29, 2014

‹‹ቤተ ጊዮርጊስ›› ከዓለም 19 አስደናቂ ቦታዎች አንዱ ሆነ



(ሪፖርተር ግንቦት 20 2006 ዓ.ም)፡-  በቅዱስ ላሊበላ ከተማ የሚገኘው ቤተ ጊዮርጊስ ውቅር ቤተ ክርስቲያን በዓለም ላይ ካሉ እጅግ አስደናቂ የተቀደሱ ሥፍራዎች ውስጥ ተካተተ፡፡

በቅርቡ ሀፊንግተን ፖስት ባወጣው መረጃ መሠረት፣ በዓለም ላይ ካሉና የተመልካችን ቀልብ ገዝተው ከተገኙ 19 ቦታዎች ውስጥ ቤተ ጊዮርጊስ አንዱ ሆኗል፡፡ 12ኛው መቶ ክፍለ ዘመን (800 ዓመታት በፊት) በአፄ ላሊበላ ከተሠሩት 12 ውቅር አብያተ ክርስቲያናት አንዱ የሆነው ቤተ ጊዮርጊስ፣ ከሌሎቹ በተለየ በተደጋጋሚ በጎብኚዎች ፎቶግራፍ የተነሳ ሲሆን፣ የበርካታ ቱሪስቶች መዳረሻ በመሆን ከተቀሩት አብያተ ክርስቲያኖች የበለጠ ዝናን የተቀዳጀ ነው፡፡

ከመሬት ወደታች ዝቅ ብሎ የተገነባው ቤተ ጊዮርጊስ በጎብኚዎች ከሚያስወድዱትና ልዩ ከሚያደርጉት አንዱ 15 ጫማ ከፍታ ያለው የፀሐይ ግብዓት የሚታይበት ቦታ መሆኑ ነው፡፡ በአጠቃላይ ኢየሩሳሌምን ተምሳሌት በማድረግ ቅዱስ ላሊበላ ከተማ ላይ የተገነቡት 12 አብያተ ክርስቲያናት ... 1978 ዩኔስኮ በዓለም አቀፍ ቅርስነት የመዘገባቸው ሲሆን፣ በወቅቱ ‹‹የኢትዮጵያ ክርስትና መገለጫና ዛሬም ድረስ የፅናት መገለጫ ሥፍራ›› በሚል ተገልጾ ነበር፡፡ 

ሀፊንግተን ፖስት ከመረጣቸው 19 መዳረሻዎች ውስጥ የፈረንሳዩ ሴንት ሚካኤል ዲጉይልሔ ቻፕል፣ ህንድ የሚገኘው አበባማ ቅርፅ ያለው ሎቱስ ቴምፕል ይገኙበታል፡፡

5 comments:

  1. በተመቅደሴን የባለጌወች ዋሻ አደረጋችሁት ማለት እኮ ይሄ ነው ጃል!

    ReplyDelete
  2. በተመቅደሴን የባለጌወች ዋሻ አደረጋችሁት ማለት እኮ ይሄ ነው ጃል!
    እንፀልይበት ወይስ በማስጎብኘት ገንዘብ እንሰብስብበት ::
    ጌታ እኮ የሚጠይቀን:ስንት Dollar አይደለም !
    ቤቴ የጸሎት ቤት ይባላል እንጅ እኮ የቱሪስት ቤት አላለም::
    የቱሪስት መስህብነታቸው ለቤተክርስትያን ምኗ ነው ግን? ገና ድሃ ነንና ሕግና ስርዓት ተጥሶ ነው እንዴ
    መበልጸግ ያለብን?
    ሁሉንም ቤተመቅደስ ለቱሪስት ከፍተን እኛ የት እንጸልይ ?

    ReplyDelete
    Replies
    1. Selam, enie gin bezih alsmamam. Bergit abyate kiritianat teturist kift sihonu mewosed yalebachew tiniqaqiewoch yinoralu. Kezih wuch gin alem kiristinachinin yemiaybet talaq menged new. Enzih abyate kiristianat le ethiopia ewunetegna kiristina quami misikiroch nachew. Egziabhere sewochin bebizu menged yastemiral. Endenezih aynet botawochin kayu behuala sewoch be wunetim tintawiwuna yeqenaw kiristina bagerachin tetebiqo endale yiredalu. Beteleyim enesu kemiawkut kiristina bemanetsatser liyu mehonun yiredalu.

      Delete
    2. እናንተ ሰፈር የሚጎበኝ ቤተ ክርስቲያን የለም መሰለኝእናንተ ሰፈር የሚጎበኝ ቤተ ክርስቲያን የለም መሰለኝ

      Delete
  3. ትክክል ነው ። ስንት ገንዘብ ተገኝ ከምንል ምን ያህል ምእመናን በጾለት አተረፍንበት ይሻላል ። ዘመኑ ከፍቶአል

    ReplyDelete